በግብጽ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት መጣሱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግብጽ የሙባረክን መንግስት ያስወገደችበት 3ኛ አመት ለማክበር በምትዘጋጅበት ወቅት ነው አምነስቲ መግለጫውን ያወጣው።

የሙባረክን መንግስት ከተወገደ በሁዋላ አገሪቱ ልትረጋጋ አለመቻሉዋን የገለጸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ በተለይም የሙርሲ መንግስት በወታደራዊ መሪዎች ከተወገደ በሁዋላ 1 ሺ 400 ሰዎች መገደላቸውን ከ500 በላይ በሚሆኑ ሟቾች ግድያ ዙሪያ ምንም አይነት ምርመራ አለመጀመሩን ገልጿል።

የሙባረክን መንግስት በማስወገድ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት ወጣቶች በእስር እየማቀቁ እንደሚገኙም ሪፖርቱ አመልክቷል። አምነስቲ የግብጽ ባለስልጣናት በግድያ የተሳተፉ የጸጥታ ሃይሎች ለ ፍርድ  እንዲቀርቡ እንዲያደርጉም ጠይቋል