ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገሪቱ ጦር ሀይሎች ቃል አቀባይ እንደገለጹት አማጽያኑ የነዳጅ ማውጫ ጉድጓዶች የሚገኙባትን ቤንቲዩን ለቀው የወጡት እኩለ ቀን ላይ ነው። የደቡብ ሱዳን መንግስት አካባቢውን መቆጣጠሩን ቢገልጽም፣ በአማጽያኑ በኩል የተሰጠ ምንም አይነት ምላሽ የለም።
መንግስት የነዳጅ ከተማዋን መቆጣጠሩ አማጽያን በመንግስት የቀረበውን ቅድመ ሁኔታ ለመቀበል ይገደዱ ይሆናል የሚል አስተያየቶች ቀርበዋል። በኢትዮጵያ መንግስትና በኢጋድ አባል አገራት ሲደረግ የነበረው ሽምግልና ውጤት አልባ በመሆኑ ሁለቱም ሀይሎች ወደ ግጭት ማምራታቸው ታውቋል።
የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት በበኩላቸው የደቡብ ሱዳን መንግስት የሪክ ማቻር ደጋፊ የሆኑትን በእስር ላይ የሚገኙትን ፖለቲከኞች እንዲፈታ ጠይቀዋል። ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሞክረዋል በማለት የሚያቀርቡትን መከራከሪያም ውድቅ መንግስታቱ አልተቀበሉትም። ለደቡብ ሱዳን መንግስት ገንዘብ ድጋፍ የምታደርገዋ አሜሪካ እንዲህ አይነት አቋም መያዙዋ ለፕሬዚዳንት ሳልቫኪር አደጋ ይነረዋል ተብሎ ተፈርቷል።
ከኢጋድ አባል አገራት ዩጋንዳ በግልጽ የሳልቫኪርን መንግስት እንደምትደግፍ አስታውቃለች።