ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ አካባቢው በማቅናት ለችግሩ እልባት ለመስጠት ጥረት እያደረጉ ነው። ይህንንም ተከትሎ በዛሬው እለት አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
አካባቢያቸውን ጥለው የወጡት የቡርጂ ተወላጆች ሙሉ በሙሉ ወደ ቀያቸው ባይመለሱም ፣ እስከ ትናንት የነበረው ግጭት በዛሬው እለት መብረዱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የዞኑ ባለስልጣናት ሆን ብለው አስነስተውታል በተባለው ግጭት አቶ ጃርሶ፣ አቶ ገልጌሎ ሁካ የተባሉት ከቦረና፣ ጨልዳሙ ጮልጌ፣ ሶማሌ ሂርጶ፣ ጎቴ ጩቴ የተባሉት ደግሞ ከቡርጂ መሞታቸውንና ጉዮ ሙሉ፣ ጅቢቻ ሎሌና ብሩ እሸቱ የተባሉት ደግሞ በድንጋይ ውርወራ ጉዳት ደርሶባቸዋል።