ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዳር እና የታህሳስ ወራትን በሙሉ በጾም በጾሎት ምእመኑ እግዚኦታ እንዲያሰማ ቄስ አለሙ ሺጣ የኢትዩጵያውያን ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ዋና ጽሓፊ በአምላክ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በኢትዩጵያ በአሁኑ ስዓት እየተሰተዋለ ላለው ችግር ፣በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ ሐገራት እንዲሁም በአለም ለሚታየውና ለሚሰማው በደል- ሀይማኖቱ በሚጠይቀው ስርዓት እጆችን ወደ አምለክ እንድናነሳ እና እንድናለቅስ የምንገደድበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡
በአረብ ሐገራት እየተፈጠረ ያለውን በደል ፤ በኢትዩጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል የሰማዩ አምላክ ምላሺ እንዲሰጣቸው ጥያቄ እናቀርባለን ሲሉ ቄስ አለሙ ሺጣ ገልፀዋል።
ፍትህ እየጠፋበት ፤ ችግር እና መከራ እየተፈራረቀባት ላለ ሃገር መፀለይ ስለሚያስፈልግ- በኢትዩጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ተቃውሞ ለመቃወመወ እና ከአምላክ ምህረት ለመለመን የሁለት ወራት የጾም እና የጾለት ጊዜ በመላው አለም እንዲደረግ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ማወጇን አስታውቀዋል።
ሐገር ስትበደል ፤ስትጎዳ እና በችግር ውስጥ ስትሆን አዋጅ ማወጅ የቤተክርስቲያኖዋ ስልጣን መሆኑን ቄስ ዓለሙ ሺጣ እስረድተዋል፡፡