ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሾፈሮቹ ለኢሳት እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የሚሄዱና ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እቃዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ተፈትሸው ለማለፍ ረጅም ጊዜ እንደሚወስዱባቸው ተናግረዋል።
ከ10 እስከ 15 ኪሎ ሜትር የሚደርስ የመኪኖች ሰልፍ መኖሩን የሚናገሩት ሾፌሮች፣ በጸሀይ ላይ በሚያደርጉት ጥበቃ በርካታ ሾፌሮች እየተጎዱ መሆኑንም ይገልጻሉ።
ፍተሻው የተጀመረው ዛሬ አራት አመት ገደማ ቢሆንም፣ ሰሞኑን የሚታየው ፍተሻ ከወትሮው በከፋ ሁኔታ እየተካሄ ነው ይላሉ ሾፌሮቹ።
በጉዳዩ ዙሪያ የጉሙሩክ ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።