ጥቅምት ፳፭(ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላው ኢትዩጵያ ተግባራዊ እንዲደረግ በኢህአዴግ ጽ/ቤት በኩል ለ14 ቀናት የሚቆይ ሰልጠና ተቀርጾ ወደ ታች በመውረድ ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡
ቅድሚያ እንዲያስተገብር ትዕዛዝ የተላለፈለት የአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች ስልጠናውን እየሰጠ ነው። ስልጠናው የኢትዩጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ወይም ኢህአዴግ የተጋድሎ ታሪክ ላይ የሚያተኩር ሲሆን አርሶ አደሮች በኢህአዴግ ላይ ተቃውሞ እያሰሙ በመምጣታቸው ስልጠና በመስጠት የማፈን ሰርዓትን ለማረጋገጥ ነው፡፡ በአሁኑ ስዓት ግንባር ቀደም እና የአንድ ለ አምስት ቡድን መሪዎችን እያሰለጠነ ያለው ኢህአዴግ ፤ በህብረተሰቡ ተሰሚነት ያላቸውን አርሶ አደር በመያዝ በሌሎች ዘንድ እየተቀጣጠለ የሚገኙውን የተቃውሞ ድምጽ ማፈን አላመው መሆኑ ተገልጹዋል፡፡
ከጥቅምት 23 የጀመረው ስልጠና እሰከ ህዳር 6 የሚቀጥል ሲሆን በእቅድ እና ትራንስፎርሜሺን ፤ በፖለቲካ አደረጃጀት ስልጠና እና ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ በቀጣይ የሚደረገውን ሃገራዊ ምርጫ ላይ መሰናክል እንዳይፈጠር እና የኢህአዴግን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እንዲያስችል አላማ ማድረጉንም እቅዱ ይፋ በሆነበት ወቅት ተገልጿል፡፡