ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀኪሙላ መሱድ የሚባለው የፓኪስታን ታሊባን መሪ የተገደለው በአሜሪካ ሰው አልባ የጦር ጅቶች መሆኑን አለማቀፍ ሚዲያዎች ቢዘግቡም እስካሁን ከአሜሪካ መንግስት በኩል የተሰጠ ማረጋገጫ የለም።
ግለሰቡ በአሜሪካ ከሚፈለጉ አሸባሪዎች ማካከል አንዱ ነው። አሜሪካ ግለሰቡ ያለበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር።
የመሱድ ምክትል ባለፈው ግንቦት ወር በተመሳሳይ መንገድ መገደሉ ይታወሳል።
የፓኪስታን መንግስት ከታሊባን ጋር ድርድር መጀመሩ በተሰማበት ወቅት ነው ግድያው የተፈጸመው።