ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ተፈሪ ፍቅሬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ከ2002 እስከ 2005 ዓመተ ምህረት ያገለገሉት አቶ ተፈሪ ፍቅሬ የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና አቃቢ ህግ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ክስ እንደመሰረተባቸው የዘገበው ፋና ነው።
የስነ ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ በክሱ ፣ ተከሳሹ ህግ እና አሰራርን በመጣስና በዜጎች መካከል ልዩነት በመፍጠርና የመንግስትን መብትና ጥቅም በሚጎዳ መንገድ በመስራት፤ በጥቅሉ ከ33 ቤቶች መንግስት ማግኘት የነበረበትን 370 ሺህ 446 ብር ተቀንሶ እንዲከራይ የማድረግ ስልጣን ሳይኖራቸው ከአሰራር ውጪ እየወሰኑ በመንግስት ላይ ጉዳይ ያደረሱና ግለሰቦችን ያለአግባብ ተጠቃሚ አድርገዋል ብሎአል።
ፍርድ ቤት የግለሰቡን የዋስትና መብት ማንሳቱም ተዘግባል።