መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አይን እማኞች እንደገለጹት ባለፉት 3 ቀናት ከ30 በላይ የሚሆኑ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ሰሜናዊ ክፍል አቅንተዋል።
መንግስት የጦር መሳሪያዎችን ለማንቀሳቀስ ለምን እንደፈለገ የታወቀ ነገር የለም። አንዳንድ ወገኖች እንደሚገምቱት በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አማጽያን የሚፈጥሩትን ስጋት ለመቋቋም ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ሊሆን ይችላል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለመነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።