መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዲስ አበባ በተለምዶ አንበሳ ግቢ ተብሎ በሚጠራው የአንበሶች ማቆያ ማእከል ውስጥ ዛሬ ከጠዋቱ 1:30 ላይ የአንበሶች መጋቢ የነበሩ ግለሰብ በ አንበሳ መበለታቸውን ራዲዮ ፋና ዘገበ።
እንደራዲዮጣቢያውዘገባአደጋው የተከሰተው በዛሬው እለት ተረኛ ተንከባካቢ የነበሩት እና አቶ አበራ ሲሳይ የተባሉትየአንበሶቹ መጋቢ፥ የአንበሶቹን ማዳሪያ እያጸዱ ባሉበት ወቅት ነው።
ከጥንቃቄ ጉድለት ባልተዘጋው በር የገባውና መጋቢውን ለህልፈተ ህይወት የዳረጋቸው አንበሳ ስሙ-ቀነኒሳ እንደሆነም ራዲዮው ጨምሮ ዘግቧል።
የግለሰቡን ህይወት ለማትረፍ በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩ የግቢው ሰራተኞች ጥረት ቢያደርጉም-ሳይሳካ መቅረቱንም ለማወቅ ተችሏል።
የሟች አስከሬን ከመንከባከቢያ ስፍራው ወጥቶ ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ተወስዷል። የዚህ አይነት አደጋ በ19 89 ዓ.ም መከሰቱ የሚታወስ ነው።