ቻይና ለመለስ ፋውንዴሽን ማስገንቢያ ገንዘብ ለገሰች

መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአቶ መለስን ፋውንዴሽን ለመገንባት መንግስትና የመለስ ፋውንዴሽን በጋራ በመንቀሳቀስ ላይ ባሉበት በዚህ ጊዜ፣ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ልኡካን ለፋውንዴሽኑ ግንባታ የሚውል 50 ሺ ዶላር ለመለገስ ቃል መግባቱዋን የልኡካን ቡድኑ መሪ ሚስተር ዛሆ ገልጸዋል።

አቶ መለስ በቻይናና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር በማድረጋቸው  ልኢካኑ አመስግነዋቸዋል። ቻይና የኢትዮጵያን የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እንደምትደግፍም እኚሁ ባለስልጣን ገልጸዋል።