መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያን ህዝብ የመብራት ፍላጎት ማሙዋላት ያልቻለውን መብራት ሀይልን ከ300 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ክፍያ የህንድ ኩባንያ ሊያስተዳድረው ነው።
ቴሌን ሲያስተዳድረው የነበረው የፈረንሳይ ኩባንያ በሺ የሚቆጠሩ ሰራተኞችን በማባረርና በቦታቸው በተለይም ከመከላከያ የመጡ ሰዎች እንዲይዙት ከማድረግ የዘለለ ነገር አልፈጸመም በሚል በሰራተኞች ሳይቀር ትችት ቢቀርብበትም፣ መንግስት መብራት ሀይልንም በተመሳሳይ መንገድ ለማስተዳደር ያወጣውን እቅድ ተግባራዊ አድርጓል።
አዲሱ ኩባንያ በርካታ ሰራተኞችን ይቀንሳል የሚል ወሬም በስፋት እየተነናፈሰ ነው። መንግስት ባለፉት 22 አመታት የሀይል አቅርቦት መጨመሩን ቢናገርም፣ በኢትዮጵያ የሚታየው የሀይል እጥረት እንደተባለው ሊቀረፍ አልቻለም።