ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ግርማ በህይወት ዘመናቸው ለሚወዷት ሀገራቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በተለያዩ ሀርፎች ያገለገሉ ሲሆን ወደ ፖለቲካው በመግባትም ትልቅ ዋጋ የከፈሉ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ ሲል አንድነት ፓርቲ ለኢሳት በላከው መግለጫ አመልክቷል።
አቶ ግርማ ወደ ተቃውሞ ጎራው ትግል የገቡት ለ1984 ዓ/ም ከፕ/ር አስራት ወልደየስ ጋር በመሆን መአህድን በመመስረት ነው። የመኢአድ አባልና የአዲስ አበባ ሰብሳቢ በሁዋላም የብርሀን ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን ከሁለቱ ፓርቲዎች ውህደት በሁዋላ ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩበት ቀን ድረስ የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ም/ቤት አብልና የፋይናንስ ቃሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ደከመን ሰለቸኝ ሳይሉ በቁርጠኝነት ትግል ማካሄዳቸውን ፓርቲው ገልጿል።
አቶ ግርማ ወልደሰንበት ለኢሳት የነበራቸውን ድጋፍም በተለያዩ መንገዶች ሲገልጹ ቆይተዋል። በቅርቡም ታመው በሚሰቃዩበት ወቅት እንኴ የኢትዮጵያ ህዝብ ኢሳትን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበው ነበር።
የኢሳት ባልደረቦች በአቶ ግርማ ወልደሰንበት ሞት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው እና ለትግል ጓደኞቻቸው መጽናናት
እነዲሆንላቸው ልባዊ ምኞታቸውን ይገልጻሉ