የአዲስ አበባ መስተዳደር ከ18 ሄክታር በላይ መሬት ማስመለሱን ገለጸ

ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስተዳድሩ በሊዝ ለማልማት መሬት ወስደው በተቀመጠላቸው ጊዜ ውስጥ ካላለሙ 284 አልሚዎች መሆኑን የኢህአዴግ ልሳን ሆነው ፋና ዘግቧል።

ባለፉት 5አመታት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ መሬት ከህገወጥ ወራሪዎች ተነጥቆ ወደ መሬት ባንክ መግባቱንም መስተዳድሩ አስታውቋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ 155 ሄክታር መሬት በመልሶ ማልማት የለማ ሲሆን፥ ከ2 ሺህ 900 ሄክታር በላይ መሬትም ለተለያዩ አገልግሎቶች በሊዝ መተላለፉ” ተገልጿል

መስተዳድሩ መሬት የነጠቃቸውን ባለሀብቶች ስም ዝርዝር ይፋ አላደረገም። በአዲስ አበባ አብዛኞቹ ንግድ ቦታዎች በተወሰኑ የመከላከያ አዛዦች እና ከስርአቱ ጋር ንክኪ ባላቸው ሰዎች መያዙ በተደጋጋሚ ተዘግቧል::  ካለፉት 15 አመታት በላይ በአዲስ አበባ ሰፋፊ መሬቶችን አጥረው በተቀመጡት በሼክ ሙሀመድ አላሙዲ ኩባንያዎች ላይም መስተዳድሩ እርምጃ ወስዶ እንደማያውቅ ይታወቃል።