በአማራ ክልል የሚደርሰው የመኪና አደጋ ጨምሯል።

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ አራት አመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ  8 ሺ 2 መቶ 46 የመኪና አደጋ የተከሰተ ሲሆን  ፣ 5 ሺ 101  ዜጎች  እጃቸውን እና እግራቸውን አጥተው ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በኢትዩጵያ በየደቂቃው ከሞት ጋር የሚጋፈጡ የመኪና አደጋ ችግር የሰው ልጅ ራስ ምታት ሁኗል፡፡

የመኪና አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመቀነስ ይልቅ ሲጨምር እንደሚታይ የገለፁት ኑዋሪዎች የመንግስት የአሰራርን ችግር በዋና ምክክንያትነት ይጠቅሳሉ።

በክልሎች የሌሊት ጉዞ የተከለከለ ቢሆንም ሁሉም የአሸከርካሪ መንጃ ፈቃዳቸውን በመያዝ ከመናህሪያ ውጭ መጫን የተከለከለከለ መሆኑን የሚያሳውቀውን ህግ ጥስው  ለአመታት በመቶዎች የሚጠጉ አደጋዎች በሌሊት ተጉዦች ላይ ጉዳት ሲደርስ የመንግስት አካላት ዝም ብለው እንደተመለከቱ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።

ከአቅም በላይ የሚጭኑ አሺከርካሪዎችን ፤ ከልክ በላይ ፍጥነት ሲመለከቱ እንዳለዩ በሙስኝነት የሚያልፉ ፖሊሶች በርካታ ናቸው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፣  ይህ የመልካም አስተዳደር ችግር ለአደጋው ቁጥር መጨመር ግንባር ቀደም ተጠቃሺ ነው ሲሉ ያክላሉ፡፡ ከ 2002 እስከ 2005 ዓም  ባለው ጊዜ ውስጥ 445 ሚሊዮን 183 ሺ 365 ብር የሚገመት  የንብረት ውድመት  በመኪና አደጋ ደርሶዋል ።

በተጠቀሰው አመት ውስጥ 2 ሺ 531 ሰዎች ህይወታቸው መቀጠፉንም ለማወቅ ተችሎአል።  9 ሺ 720 ዜጎችም ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡ ቀላል የአካል ጉዳት የሚባለው  አንድ እጅ ወይም አንድ እግር እስከማጣት የሚደርስ ነው።