ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ህብረት በጤና ጉዳይ ላይ ለመመካከር በናይጀሪያ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ሰብሰባቸውን ሳይጨርሱ ወደ አገራቸው የተመለሱት ፣ አለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የናይጀሪያ መንግስት ይዞ እንዲያስራቸው አቤቱታውን ለፍርድ ቤት ካቀረበ በሁዋላ ነው።
ፕሬዚዳንቱ ሰኞ እለት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ በድንገት አገሪቱን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል።
ፕሬዚዳንት በሽር ናይጀሪያ ሲገቡ የናይጀሪያ መንግስት የክብር አቀባበል አድርጎላቸው ነበር። የናይጀሪያ አለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድቤት ጥምረት ፕሬዚዳንቱ ታስረው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ለአገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ እንደነበር ዘገባዎች አመልክተዋል።