ግንቦት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ባለፈው ዓመት ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም የጣለው ከባድ ዝናብ ከ 3000 በላይ ኖሪዋችን ማፈናቀሉንና ከ 15 ሰዎች በላይ መግደሉን ያስታወሱት ነዋሪዎች ፣ የከተማው አስተዳደር ከአምናው ትምህርት ለመውሰድ ባለመቻሉ ማዘናቸውን እየገለጹ ነው።
የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሺን ችግሩን ለማስወገድ ለከተማ አስተዳደሩ ሩብ ሚሊዩን ብር ቢለግስም ገንዘቡ የት እንደገባ እንደማይታወቅ ምንጮች ገልጸዋል።
ችግራችንን ለማሰወገድ መንግስት ምንም ዓይነት መፍትሄ አልሰጠንም፡፡ በስጋት የምንኖርበት በማገር እና በጣራ ላይ ተንጠልጥን መፍትሄ አልባ መንግስት ዋስት የሌለው ሁኖብንል በማለት ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።