ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በጣና ሃይቅ ላይ ከ 100 በላይ መንገደኞችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ የነበረ ፋሲለደስ እየተባለ የሚጠራው ጀልባ በማእበል ተመቶ በመስጠሙ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ከ10 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸን ለማወቅ ተችሎአል። የአደጋው መንስኤም ከባድ ዝናብን ተከትሎ በተከሰተ ማእበል መሆኑን ነው አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ የድርጅቱ ሰራተ ለኢሳት የገለጹት ። ይሁን እንጀ ኢሳት ትክክለኛውን ምክንያት ለማጣራት ሙከራ እያደረገ ነው። በባህርዳር ከተማ ዝናብ አለመዝነቡን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያሳያል
አደጋው የደረሰው አመታዊ የክርስቶስ ሰምራን የንግስ በዐዓል አክብረው ከደልጊ ወደ ባህርዳር በማምራት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ነው።
በባህርዳር ከተማ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ አደጋ ሲደርስ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።