ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ለረጂም ዓመታት በራስ ቴአትር በድምጻዊነት ስታገለገል የቆየችው አበበች ደራራ ባደረባት ህመም ሳቢያ በእስራኤል ግንቦት 8 ፣ 20005 ዓም አርፋለች። ድምጸ መረዋዋ አበበች ደራራ ለበርካታ አመታት ከሽታዋ ጋር ስትታገል መቆየቷን በቅርብ የሚያውቁዋት ሰዎች ተናግረዋል። የአበበች ደራራ የቀብር ስነስርአት በኖረችበት የቴል አቪቭ ከተማ መፈጸሙን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ኢሳት ለአርቲስ አበበች ደራራ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።