መጋቢት ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የሳውዲ አረብያ ም/ል የመከላከያ ሚ/ር በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባውን የሀይል ማመንጫ አስመልክቶ የሰጡት ምገለቻ የሀገሪቱን መንግስት አቋም እንደማይገልፅ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጹን የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ፋና ብሮድካስቲን ዘግቧል።
የኢትዮጵያና የሳዑዲ አረቢያ የሁለትዮሽ ግኑኝነት መከባበርንና የጋራ ተጠቃሚነትን እንዲሁም አንዱ በሌላው ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ጣልቃ አለመግባትን መሰረት ያደረገ መሆኑን የገለጠው ድርጅቱ፣ በቅርቡ የሳውዲ አረቢያ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ቢን ሱልጣን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በታችኛዎቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል የሚል መግለጫ መስጠታቸው አይመለከተኝም ብሎአል።