በመላ አገሪቱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ አሰሙ

የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- የድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች በነደፉት መርሐግብር መሰረት በአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ተቃውሞዎች የተደረጉ ሲሆን፣ መንግስት የሙስሊሙ ጥያቄ ከእጁ እየወጣ መውጣቱን የሚያመለክት ሆኗል።

በመቀሌ፣ በመቱ፣ በጅጅጋ፣ በአፋር፣ በጅማ ፣ ወልቂጤ፣ ጎንደር ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞዎች ተነስተዋል።

በአዲስ አበባ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ” መሪዎቻችን ይፈቱ ድምጻችን ይሰማ በቤታችን ሰላም ስጡን” የሚሉ መፈክሮችን አሰምቷል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ለመከፋፈል መንግስት በእየለቱ የሚያሰራጨው ፕሮፓጋንዳ ሙስሊሙን በቁጭት እንዲነሳ እያደረገው መሆኑን ታዛቢዎች ይገልጻሉ።

በመላው አገሪቱ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚያሰሙት ተቃውሞ ብዙዎችን እንዳስደመመ ቀጥሎአል።