የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በመቀሌ ከተማ የላጪ ሰፈር ነዋሪዎች በውሀ እና በመብራት እጦት ለ ዓመታት እየተንገላታን እንገኛለን ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል
የላጪ ሰፈር ነዋሪዎች ለኢሳት ዘጋቢ እንደገለፁት ማዘጋጃ ቤቱ በሰጣቸው ቦታ ቤት ሠርተው ከገቡ ሁለት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፤እስካሁን ድረስ ውሀ እና መብራት ሊገባላቸው አልቻለም።
ችግራቸውን በተደጋጋሚ ለሚለከተው የመንግስት አስተዳደር ቢያቀርቡም ምንም ዓይነት መፍትሔ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በመቀሌ ከፍተኛ ንፁህ መጠጥ ውሀ ችግር እንዳለ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
ብዙዎቹ የከተማዋ ነዋሪዎች በንፁህ የመጠጥ ውሀ እጦት በሚሰቃዩበት ጊዜ የ ኢፈርት ሀላፊዎች እቤታቸው ድረስ የውሀ ማጣሪያ እንደገባላቸው መዘገባችን ይታወሳል።
እንዲሁም ከፍተኛ የህወሀት ሹማምንት ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኝ ነፋሻማ ቦታ ላይ በብዙ ሚሊዮን ብር ወጪ የተሠሩ ቬላዎችን ያቀፈ አፓርታይድ የተሰኘ እንደገነቡ በተደጋጋሚ መዘገቡ አይዘነጋም።