የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ካናዲያን ኤክስፕሎረር አፍሪካን ኦይል የተሰኘው ኩባንያ አዲስ መሬት የተሰጠው በምስራቅ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው። ኤክስፕሎረር አፍሪካ በደቡብ ኦሞ የነዳጅ ፍለጋ በማካሄድ ላይ ካለው ቱሎው ኦይል ጋር በሸርክና የሚሰራ ድርጅት ነው።
ቱሎው ኦይል በደቡብ ኦሞ የሚያካሂደው አሰሳ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ይናገራል። ድርጅቱ ተሳክቶለት ነዳጅ ማውጣት ከጀመረ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል።
ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግስት ድርሻ ከ10 በመቶ የማይበልጥ ቢሆንም በአገሪቱ የሚታየው ከፍተኛ ሙስና ግምት ውስጥ ሲገባ፣ ህዝቡ ከነዳጁ ሀብት ብዙም ተጠቃሚ ይሆናል ተብሎ እንደማይታሰብ ተንታኞች ይናገራሉ።
በደቡብ ኦሞ ዞን የአንድነት ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ስለሺ ጌታቸው በአካባቢያቸው ነዳጅ መገኘቱን የኩባንያዎቹ ባለስልጣናት በተለያዩ መንገዶች እየገለጡ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ መንግስት ግን እስካሁን ይፋ ለማድረግ አልፈቀደም። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት በአካባቢው ነዳጅ መኖሩንና አለመኖሩን የሚያመልክት ሪፖርት ይፋ እንደሚያደርግ ታውቋል።