ፕሬዚዳንት ሞርሲ ምርጫ እንዲደረግ አዘዙ

የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የግብጹ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሞርሲ ጥሪውን ያቀረቡት በአገሪቱ የሚታየው ተቃውሞ እያየለ መምጣቱን ተከትሎ ነው።

የአስመራጮች እጥረት በመፈጠሩ ምርጫው ከሚያዚያ እስከ ሰኔ ድረስ ባለው የጊዜ ገደብ እንደሚከናወን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ሞርሲና ፓርቲያቸው ምርጫው በየጊዜው የሚካሄደውን የመንገድ ላይ ተቃውሞ ያስቀራል ብለው ያምናሉ።

.ግብጽ በሊበራል ዲሞክራሲ አቀንቃኞችና በሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ደጋፊዎች ስትታመስ መቆየቷ ይታወቃል።

ፕሬዚዳንት ሞርሲ የግብጽን አብዮት ቀልብሰዋል እየተባሉ ሲተቹ ሰንብቷል። የአሁኑ ውሳኔያቸው ለአገሪቱ የተሻለ ነገር ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።