በደቡብ ክልል በተለያዩ ከተሞች የተነሳ የማጅራት ገትር ወረርሽኝ የሰው ህይወት እያጠፋ መሆኑ ተገለጠ::
ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የኢሳት ምንጮች ከሀገር ቤት እንዳስታወቁት ከሆነ በአርባ ምንጭ ብቻ 6 ሰዎች በማጅራት ገትር ወረርሽኙ ሞተዋል::
በዚህ መረጃ መሰረት በጨፌና በላሉ አካባቢዎችም ወረርሽኙ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎችን መግደሉን አመልክቶል::
በአዋሳ ከተማም በማጅራት ገትር ወረርሽኙ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ በሀደሌ ጤና ጣቢያ በጊዜያዊ የድንኮን መኝታ ተዘጋጅቶ ሰዎች በህክምና እየተረዱ ይገኛል ተብሎል::
በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችል የህክምና ርብርብና መድሀኒት ግን እንደሌለ ምንጮች አስታውቀዋል::