የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሁለት ለዜሮ በሆነ ውጤት ተሸነፈ

ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ዋልያዎች የመጀመሪያውን ግማሽ ጨዋታ ዜሮ ለዜሮ ቢጨርሱም፣ በ79ኛው ደቂቃ ላይ  ናይጀሪያዎች ያገኙነትን የፍጹም ቅጣት ምት በቪክቶር ሞስስ አማካኝነት አግብተዋል። የናይጂሪያ ቡድን 10 ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ሌላ የፍጹም ቅጣት አግኝተው ሁለተኛውን ጎል በድጋሜ በሞስስ አማካኝነት አስቆጥረዋል። ጥፋቱን የሰራው ጎል ጠባቂው ሲሳይም በቀይ ወጥቷል።

ብሄራዊ ቡድኑ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ካደረገው ጨዋታ ጋር ሲተያይ ዛሬ የተሻለ ጨዋታ አሳይቶ ነበር።