ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዚህ መሰረት ማህበሩ ከተቆቆመበት ጀምሮ ማህበሩን በፕሬዚዳንትነት በመሩት በዶ/ር ሼክስፔር ፈይሳ ምትክ አቶ አበበ ሀይሉ ም/ፕሬዚዳንት ደግሞ ዶ/ር ሰለሞን ረታ አድርጎ ሠይሞል::
በተዋረድ በዋና ጸሀፊነት፣ በህዝብ ግንኙነት፣ በፋይናንስ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንትና በመድረክ አስተባባሪነት በቀድሞ የስራ አስፈጻሚዎች ምትክ አዲስ ተመርጦል::
የቀድሞ የማህበሩ የስራ አስፈጻሚ አባላት ለአዲሶቹ ተመራጮች የስራና የንብረት ርክክብ የፈጸሙ መሆኑን የገለጠው የማህበሩ መግለጫ የኢትዮጵያን ማህበራት፣ ተባባሪ አባላት፣ የቦርድ አባላት፣ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲዎች ለአዲሱ አመራር የተለመደ የስራ ትብብር እንዲያደርጉላቸው ጠይቆል::
ማህበሩ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው በዚህ መግለጫ የአድዋን ድል አስመልክቶ በማርች ሁለት ለሚኖረው ዝግጅት እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን በዋሽንግተን ዲሲም ሶስተኛው ፊስቲቫል በሰመር እንደሚካሄድ አስታውቆል::
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር የኢትዮጵያን ቅርሶችና ታሪኮን መጠበቅና ማስተዋወቅ ከአላማዎቹ በዋናነት ይዞ ለተግባራዊነቱ የሚንቀሳቀስ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል::