ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ሱዳን ትሪቡንን ዋቢ ያደረገው ኦል ኣፍሪካ አንደዘገበው የመሴኔቱ ኣባላቶችየደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬርን ነዳጃቸውን ለኣለም ገበያ ለማቅረብካርቱምን መጠቀምና መጠበቅ አንደሌለባቸው ኣሳስበዋል::
ባለፈው ኣመት ግንቦት ወር የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ሚኒስቴር ስቲፍን ዶ ለዎልስትሪት ጆርናል አንደገለጹት ቢያንስ ቢያንስ የነዳጅ ምርታቸውን 10 በመቶወይም ሰላሳ አምስት ሺ በርሜል በቀን በከባድ መኪና (በቦቴ) ኢትዮጵያንናኬንያን አቆራርጠው በጅቡቲ ለአለም ገበያ ለማቅረብ አቅደዋል::
በዚህ ሳምንት የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባን የጎበኙት የአሜሪካ የሴኔት አባላቶች የሰሜን ሱዳን የነዳጅ ዘይት ማጎጎዝን የማስ ፉከራ ትርጉም የለውም ካሉ በሆላ ነዳጃቸውን ለአለም ገበያ ለማቅረብ ከባድ መኪናንና ኢትዮጵያን መጠቀም አለባቸው ሲሉ አስታውቀዋል::