ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ አበበ ገላውን ለመግደል ተጠንስሶ የነበረውና በ ኤፍ.ቢ.አይ መርማሪዎች የከሸፈው የግድያ ሙከራ ዜና በርካታ ኢትዮጵያውያንን እያስቆጣ ነው።
በጋዜጠኛ አበበ ገላው ላይ የታቀዳውን የግድያ ሙከራ የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ማክሸፉን ተከትሎ በቦስተን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አክቲቪስቶች ሌሎች የህውሀት ጉዳይ አስፈጻሚ ያሎቸውን ሰዎችና ስም ዝርዝራቸውን ለኢሳት አድርሰዋል::
እነዚህ ግለሰቦች በተለይ በሀገር ቤት ንብረት ያፈሩ ኢትዮጵያዊያን በየትኛውም ህዝባዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዳይሳተፉ በመከላከል ተሳትፈው ሲገኙም በማስጠንቀቅ ነጻነታቸውን እንደሚገድቡ ለኢሳት በላኩት ሪፓርት አመልክተው::
በዚህ ረገድ በዋናነት የተጠቀሱትና ፎቶግራፋቸውና ስማቸው የሰፈረው ሚካኤል በርሄ ፡ሀይሌ ኪሮስ ፡ሱሌማን አህመድ ፡ ብዙነህ ሀጎስ ፡ሀብቶም ደስታ ገብሩና ማህሌት በርሄ ናቸው::
በጋዜጠኛ አበበ ገላው ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ በአሜሪካ የፌደራል የምርመራ ቢሮ መክሸፉን ተከትሎ ዜናው አብይ መነጋገሪያ ሆኖ ቀጥሎል:
ዜናው፤ በተለይ ፌስቡክና ትዊተርን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ መገናኛዎችን በሚጠቀሙ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።
ኢትዖ ያውያኑ በፌስ ቡክ ከሰጧቸው አስተያዬቶች መካከል፦<<በአበበ ገላው ህይወት ላይ ለሚቃጣ ማናቸውም ጥቃት ተመጣጣኝ አጸፋ እንመልሳለን!የቁርጥ ቀን ልጃችንን አበበ ገላውን ለመግደል ሲያሴሩ የተያዙት ወደ ጓንታናሞ ወርደው የሰው ልጅ ህይወት ውድና ክቡር መሆኑን እስኪረዱ ድረስ ፍትህን ይቀበሉ! እኔም አበበ ገላው ነኝ!>>የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል።
ዜናው በ አገር ቤት ጭምር ሰፊ መነጋገሪያ እንደሆነም የ ኢሳት ዘጋቢዎች አመልክተዋል።
በአሜሪካ ሀገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖረውና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ብሎ የሚጠራው ድርጅት አባል እና ሰላይ እንደሆነ የሚታመነው ግኡሽ አበራ በመባል የሚጠራ ግለሰብ፤ ጋዜጠኛ አበበን ለመግደል በማሴር ሶስት የወንጀሉ ተባባሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን መመልመሉ ንና ድርጊቱን ለመፈጸም መሰናዶ ማድረጉን የFBI መሪማሪዎች ደርሰውበት ሴራውን በግዜ እንዳከሸፉት መዘጋችን ይታወሳል።