ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የ 104 አመት የዕድሜ ባለጸጋ ኢትዮጵያዊ ላለፉት 12 አመታት ያላማቆረጥ በዴንቨር በሚገኝ አንድ ሞል ለ 2 ሰአታት የእግር ጉዞ ያደርጋሉ::
ጡረተኛው የፋርማሲ ባለሙያ የ 104 አመቱ ኢትዮጵያዊ አቶ ሚካኤል የጥሻ ወርቅ ለረዥም ዕድሜና ለሙሉ ጤንነት ሚስጥሩ መራመድ መንቀሳቀስና መጎዝ ነው ይላሉ::
በዴንቨር ቼግሪ ቻጊ የገበያ አዳራሽ ላለፉት 12 አመታት በትንሹ ለ 2 ሰአት ያህል የእርምጃ ስፖርት ሲሰሩ በልጅ በአዛውንቱ የሚታወቁት አቶ ሚኪ 10 አይነት ቆንቆ ይናገራሉ::
ፈረንሳይኛ ጣሊያንኛ ጨምሮ ስፓንሽኛ ሳይቀር እዚህ አሜሪካ ከመጡ ማዳመጥና መናገርን ችለዋል::
አቶ ሚካኤል ወደ አሜሪካ በመምጣት ጥገኝነት የጠየቁት የዛሬ 35 አመት ነበር ዛሬ በ 104 አመታቸውም በሙሉ ጤንነትና ጥንካሬ በዴንቨር ሞል ውስጥ እያንጎራጎሩ ሲራመዱ በየቀኑ ይስተዋልሉ::
የምበላው በቀን አንዴ ነው የሚሉት አቶ ሚካኤል የሰው ልጅ 10 ከመቶውን ከምግብ ያገኛል የቀረውን 90 በመቶ ፈጣሪ ይሞላዋል የሚል እምነት አላቸው::
ዩ ኤስ ኤ ቱ ደይ እንደዘገበው በሞሉ ውስጥ ላለፉት 12 አመታት የሚያዮቸው ልጅና ወጣት ፡ አዛውንትና ጎልማሳ አቶ ሚካኤልን ያውቆቸዋል ይወዶቸዋልም ብሎል::