ታህሳስ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በከተማዋ በቆሚነት ደርድረውና እያዞሩ ጋዜጣና መጽሄት የሚሸጡ በመከልከላቸው ህዝቡ ጋዜጣ ማግኘት አለመቻሉን የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎችና የቅርብ ምንጮች ያላቸውን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቦል::
ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁና በአካባቢው ጋዜጣና መጽሄት በመሸጥ የሚተዳደሩ ወጣቶች የጠቀሰው ዘገባ የከተማዋ ወያኔ ወረዳ ንግድና ኢንዱስትሪ አስተዳደር ስራው ህገወጥ መሆኑ ተገልፆላቸው ከታህሳስ 5፣2005 ጀምሮ በአካባቢው የገል ጋዜጣና መጽሄት የመሸጥ ስራ እንዳይሰራ መታገዱን አመልክቶል::
ይህንን ትእዛዝ ተላልፋችሁ ጋዜጣና መጽሄት እያዞራችሁ ተገኝታችሆል የተባሉ አምስት ወጣቶች በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው የታወቀ ሲሆን ሲያዞሩት የነበረው ጋዜጣና መጽሄት መወረሱ ተዘግቦል::