ታህሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ወጣቶች ያስተላለፉትን ጥሪ ተከትሎ በቃሊቲ እና በደሴ እስር ቤቶች ከእስረኞች ቤተሰቦች ውጭ አዳዲስ ተጠያቂዎችም መታየታቸውን አዘጋጆች ገልጸዋል።
ወደ ቃሊቲ የተጓዘው ህዝብ እስረኞች የታሰሩበትን ቦታ ባለማወቁ ሲቸገር መታየቱን አዘጋጆች ገልጸዋል። ምንም እንኳ በቃሊቲ የጠበቁትን ያክል ህዝብ ባይገኝም፣ ለመነሻ በቂ መሆኑን አዘጋጆች ገልጸዋል። “ሁሉም ነገር ከዜሮ ነው የሚጀምረው” ያሉት አዘጋጆች ” የእሰረኞች ቤተሰቦች፣ በጠያቂዎች ብዛት ተገርመው እንደነበርም” ገልጸዋል።
አዘጋጆች ህብረተሰቡ በሂደት ስለሚወስደው እርምጃ ጥሪ እንደሚያቀርቡም ገልጸዋል።