ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በስደት ሌላ ሀገር የምንሄድበት ሁኔታ ካለ ይመቻችልን ሲሉም ጥያቄ አቀረቡ።ቤታቸው በመንግስት ትእዛዝ ፈርሶ ከአደባባይ ከሚገኙ የንፋሰልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ነዋሪዎች ጋር ኢሳት ባደረገው ቃለ-ምልልስ ነዋሪዎች እንደገለፁት ምን ማድረግ አለብን ብለን በችግሮቻችን ላይ ለመወያየት ስለሞከርን የመንግስት ታጣቂዎች የናንተ ጥያቄ ሌላ ነው ሲሉ በትነውናል ብለውናል።
ለመንግስት ባለስልጣናት አቤት ለማለት ባንዲራ ይዘን በወጣን ጊዜ ባንዲራውን በመንጠቅ ኢትዮጵያውያኞች አለመሆናችንን ነግረውናል ያሉት ነዋሪዎቹ አሁን ካሉበት የስቃይ ኑሮ ለመላቀቅ በስደት የምንሄድበት ሀገር ይመቻችልን ሲሉ መንግስትን ጠይቀዋል።
በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ መንግስት ባደረገው የቤት ማፍረስ ዘመቻ ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።