ህዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የድጋፍ ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ሱፊያን አህመድና የአውሮፓ ኅብረት የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተርና የአፍሪካ ካሪቢያን ፓስፊክ አስተባባሪ ፍራንሲስካ ሞስካ ናቸው።
ድጋፉ የወጪ ምርቶችና በተመረጡ ኢንቨስትመንት መስኮች በቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፣ ጨርቃጨርቅ ፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያና መድኃኒት ፋብሪካዎችን በቴክኖሎጂ ሽግግር ፣ በልምድና ክህሎት እንዲሁም የገበያ ልማትን በማጠናከር ተወዳዳሪነታቸውን ለማጠናከር እንዲሁም በቢዝነስ ፣በሥራ አመራርና በፈጠራ ሥራ ለግሉ ዘርፍና ለመንግሥት ተቋማት ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮ-አውሮፓ የቢዝነስ ትምህርት ቤት ለመክፈት ይውላል ተብሎአል።