መንግስት 6 የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ሊያዞር ነው

ጥቅምት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ እንደዘገበው ወደ ግል ከሚዞሩት ድርጅቶች መካከል 600 ሄክታር የሚሸፍነው በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው አርባ ጉጉ የቡና ተክል ይገኝበታል።

መንግስት ከስድስቱ የልማት ድርጀቶች 1 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱም ታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የ5 አመቱን እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት  የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል በማዞር የገንዘብ እጥረቱን ለመቅረፍ እየሞከረ ነው።

መንግስት አምና የሜታ ፣ የሀረርና በደሌ ቢራ ፋብሪካዎችን ለእንግሊዙ ዲያጎና ለሆላንዱ ሀይነከን ኩባንያዎች በ485 ሚሊዮን ዶላር መሸጡ ይታወሳል።

ከመንግስት ወደ ግል የሚዞሩት ኩባንያዎች ከፍተኛ የሙስና ምንጭ መሆናቸው ይነገርላቸዋል።