ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው ፤በአዲስኢትዮጵያውያን ያልተሳተፉበትን የኢንቨስትመንትኮንፈረንስ ያዘጋጁት አበባ የተካሄደውንና ፤ተቀማጭነቱ በስፔን የሆነው ሲንጉላ ሪስ አድቫይዘርስ የተባለ ኩባንያ – “ዋይ.ኤች.ኤም ኮንሰልቲንግ” ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው።
ባለፈው ሳምንት ለሦስት ቀናት በሒልተን ሆቴል በተካሄደው የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ አንድም የኢትዮጵያ ኩባንያ አልተሳተፈም።
በጣም አስገራሚው ነገር ፤ስብሰባው የተዘጋጀው ኢትዮጵያን ጨምሮ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶቻቸው ገንዘብ የሚፈልጉ የአፍሪካ ኩባንያዎችን
ከአውሮፓና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከመጡ የገንዘብ ተቋማት ጋር ለማገናኘትና ለማወያየት ታስቦ እንደሆነ የዋይኤችኤም ኮንሰልቲንግ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ያሬድ ኃይል መስቀል መገለጹ ነው።
ክሬዲት ስዊዝ፣ ባንካ ኤስፔራ፣ ሶሳይቲ ጄነራል ፕራይቬት ባንኪንግ ኦፍ ፍራንስ፣ ሼቭሮን ናይጄሪያ ፔንሽን ፈንድ፣ ጀርመን ኢንቨስትመንት ኤንድ ዴቨሎፕመንት ባንክ፣ ገልፍ አፍሪካን ባንክ፣ ኤስኮም ፔንሽን ኤንድ ፕሮቪደንት ፈንድ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና ደች ዴቨሎፕመንት ባንክ በስብሰባው ላይ ከተሳተፉ በበርካታ ገንዘብ አቅራቢ ድርጅቶች መካከል ይገኙበታል፡፡
በጉባዔው ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች በርካታ ገንዘብ ፈላጊ ኩባንያዎች የተገኙ ሲሆን፤ በተለይ ከኬንያ፣ ከደቡብ አፍሪካና ከናይጄሪያ የመጡ ኩባንያዎች ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፈንድ እንዳገኙ ተገልጿል፡፡
“አዲስ አበባ ላይ በተካሄደ ኮንፈረንስ ዘጠና ያህል የውጪ ኩባንያዎች ሲሳተፉ አንድም የኢትዮጵያ ኩባንያ ያልተሳተፈበትን ምክንያት ምንድነው?” ተብለው የተጠየቁት አቶ ያሬድ፣ ከግንዛቤ ማነስና የተሳትፎ ክፍያውን በመፍራት ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
‹‹ለተለያዩ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች የግብዣ ወረቀት በመላክ ብቻ ሳይሆን በየቢሮዋቸው በአካል በመሄድ ስለስብሰባው ለማስረዳት ብንሞክርም፣ አንድም ኩባንያ ክፍያውን ከፍሎ በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ አልሆነም፤›› ብለዋል አቶ ያሬድ፡፡
በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ አንድ የኩባንያ ተወካይ 5,000 ዩሮ መክፈል ይጠበቅበታል ያሉት አቶ ያሬድ፣ “ገንዘቡ ብዙ ሊመስል ቢችልም፤ ከስብሰባው ከሚገኘው ጥቅም አንፃር ሲታይ ግን ምንም ማለት አይደለም” ብለዋል፡፡
ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች በዚህ ጉባዔ ተጠቃሚ ባይሆኑም፣ ጉባዔውን በየዓመቱ ለማካሄድ በመታቀዱ ለወደፊቱ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡