ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የጸጥታ ቢሮ ሀላፊው አቶ አብዱላሂ የሱፍ ይህን የተናገሩት የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ( ኦብነግ) ከመንግስት ጋር ያደርግ የነበረውን ድርድር አቋርጦ በመውጣቱ እንዲያወግዝ ሰልፍ ለወጣው ህዝብ ነው።
የጅጅጋ፣ ደጋሀቡር፣ ቀብሪደሀርና ጎዴ ህዝብ ኦብነግ ከመንግስት ቀረበለትን የድርድር ጥያቄ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኑ በሰላማዊ ሰልፍ እንዲያወግዝ ሰሞኑን ሲቀሰቀስና ሲገደድ እንደነበር አንድ የአካባቢው ተወላጅ ለኢሳት ገልጠዋል።
የክልሉ የጸጥታ ሃላፊ ኦብነግ ተደምስሷል በማለት ኦብነግን ለማውገዝ ለተሰበሰው ህዝብ መናገራቸው ሰልፈኛውን ግራ አጋብቶ እንደነበር ተወላጁ ገልጧል።
“ኦብነግ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል ከተባለ ኦብነግ የድርድር ጥያቄውን አልቀበልም ስላለ አውግዙ ተብሎ” ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጣ ማድረግ ለምን አስፈለገ ሲሉ ጠይቀዋል።
መንግስት እንደ ትልቅ ድል ተመልክቶት የነበረው ከኦብነግ ጋር የሚያደርገው ድርድር ድርድር መቋረጡን መዘገባችን ይታወሳል።