ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ለኢሳት እንደገለጡት ቤንጋዚ እየተባለ በሚጠራው የሊቢያ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ከ250 በላይ ኢትዮጵያውያን ከፍተና እንግልት እየደረሰባቸው ነው።
ኢትዮጵያውያኑ እንዳሉት የተበባሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳያቸውን ለመከታተል ፈቃደኛ ባለመሆኑ፣ በቅርቡ የጋዳፊን መንግስት በመጣል በተሳተፉት አክራሪዎች እንግልት እየደረሰባቸው ነው።
አክራሪዎቹ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ያለፍላጎታቸው የእስልምና እምነትን እንዲከተሉ ከማስገደድ ጀምሮ፣ ሴቶችን አስገድደው ይደፍራሉ።
የአለማቀፉ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያን በፍጥነት እንዲደርሱልን እንማጸናለን በማለት ኢትዮጵያውያኑ ጠይቀዋል።
በስደት ወደ አረብ አገራት የሚጎርፈ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግፍ እየጨመረ መምጣቱን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሞሮኮ የተነሳችና በርካታ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በመስመጧ 14 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።
ቢቢሲ የሟቾች አገር በውል አለመታወቁን ገልጣል። ከ70 በላይ ሰዎችን አሳፍራ ትጓዝ ከነበረቸው ጀልባ እስካሁን በህይወት ለማትረፍ ተቻለው 17 ሰዎችን ብቻ ነው።