ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከፍተኛ ካድሬዎች በመሩት በነዚህ መድረኮች የመለስን ራዕይ ማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ
ሰራተኛው ግልጽ አቋም እንዲኖረው በይፋ ተነግሮታል፡፡
አቶ መለስ ካረፉ በኃላ ከከፍተኛ ካድሬው ወደ መካከለኛና ወደ ዝቅተኛ አመራር ሲንከባለል የነበረው ይህው ውይይት
የመንግስት ሰራተኞችንም ማካተቱ፣ ለሲቪል ሰርቪሱና ፖለቲካው መደበላለቅ ትልቅ መገለጫ መሆኑን ያነጋገርናቸው
ሰራተኞች አስረድተዋል፡፡
አንድ የማዘጋጃ ቤቱ ሰራተኛ እንደተናሩት የተቀጠሩት የመንግስትን ተለይቶና ተለክቶ የሚታወቅ ስራ ለመስራት
መሆኑን በማስታወስ፣መመዘንም፣መጠየቅም ያለባቸው በዚሁ ስራቸው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ራዕይ አስፈጻሚ
ናችሁ መባሉ ግራ እንዳጋባቸው ጠቅሰዋል፡፡ ሰራተኛው የአቶ መለስን ራዕይ ለማስፈጸም በቅድሚያ ራዕዩ ምን
እንደሆነ እንደማያውቁ፣ አስረጂዎችም ስለዚህ ጉዳይ ያሉት ነገር አለመኖሩን ጠቅሰዋል፡፡
ራዕዩ ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ “ራዕዩን እናሳካለን” በሚል የካድሬዎች መፈክር ለመስማት ጊዜ ማጥፋታቸው እንዳሳዘናቸው አስረድተዋል፡፡ የአቶ መለስን ራዕይ ለማሳካት በሚል የኢህአዴግ አራቱም ፓርቲዎች ካድሬዎቻቸውንና አባሎቻቸውን በማንቃት ስራ
ተጠምደው መክረማቸው የሚታወስ ነው፡፡