ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የትምህርት ሚኒስቴር ባስተላለፈው ትእዛዝ መሰረት በመላ አገሪቱ የሚገኙ ተማሪዎች የፈታችን ሰኞ በሚደረገው የባንዲራ ቀን በአል ላይ ጥቁር ሪባን በማሰርና የታላቁን መሪ የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ ከፍ አድርጎ በመያዝ በአሉን እንዲያከብሩ ትእዛዝ አስተላልፎአል።
በመጪው ጥቅምት 19 የሚከበረው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ራዕይ ለማሳካት ቃል ኪዳናችንን በማደስ የምናከብረው ነው ሲሉ የተወካዮች ምከር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባ ዱላ ገመዳ መናገራቸው ይታወሳል።
በዓሉ በፌዴራል ደረጃ በአዲስ አበባ ስቴዲየም የሚከበር ሲሆን በክልሎች እና በከተማ መስተደድሮችም በተመሳሳይ ሰዓት ይከበራል።