ወጣቱ ትውልድ በአንድነት ለሀገር እድገት እንዲቆም ጥሪ ቀረበ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አዲሡ ትውልድ ተቻችሎና ተከባብሮ ለሃገሩ በአንድነት እንዲቆምና እንዲሠራ አንጋፋው ኢትዮጲያዊ ዶክተር አክሊሉ ሐብቴ ጠሪ አቀረቡ።

በሐገር ቤትና በውጭ ሐገር የሚገኙ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶችን ለመሸምገል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉንም ዶር አክሊሉ ሐብቴ አብራርተዋል።በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የዛሬው አዲስ አበባ ፕሬዝዳንት የነበሩት በኋላም በሚንስትርነት እንዲሁም በአለም ባንክና በዩኒሴፍ ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት ያገለገሉት ዶር አክሊሉ ሐብቴ ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ ይየአባቶቹን የሽምግልና ሂደት ለማሳካት መንግስት ከጉዞ ሰነድ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ድጋፉን እንዲሰጥም ጥሪ አቅርበዋል።