ጥቅምት ፲፬ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በተባበሩት አረብ ኤሚሬት አቡዳቢ፤ በአሰሪዋ ከፎቅ የተወረወረችው የ20 አመት ኢትዮጵያዊ እግር ላይ በደረሰው ጉዳት በአልጋ መቅረቷ ተነገረ። በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ቆንስላ የወጣቷን ፓስፖርት ወስዶም እንዳትንቀሳቀስ አግዷታል። ወጣቷ በአቡዳቢ ፍርድ ቤት የተወሰነላትን 500 ሺህ ድርሀም የጉዳት ካሳ ክፍያ ማግኘት አልቻለችም።
ወጣት መዲና መሀመድ ከአመት በፊት አቡዳቢ ገብታ እራሷንና ቤተሰቧን ሰው ቤት በመስራት ለመርዳት የወጠነችውን ሀሳብ ከ15 ቀናት በላይ ልታዘልቀው አልቻለችም።
በተቀጠረች በ15 ቀኗ አሰሪዋ ከፎቅ ላይ ወርውራ የጣለቻት ሴት፤ ዛሬ እግሯ ከቀን ወደቀን እሰለለ መጥቷል፤ መራመድና መንቀሳቀስም አልቻልኩም ስትል፤ ከኢሳት ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ ገልጻለች።
መዲና መሀመድ አካል ጉዳተኛ ሆና መጠጊያ ባጣች ግዜ አንድ ኢትዮጵያዊ ሴት አስጠግታት እንዳሳከመቻት የገለጸችልን ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊቷ ጠበቃ ገዝታ በአሰሪዋ ላይ ክስ በመመስረት 500 ሺህ ድርሀም የጉዳት ካሳ ለማስወሰን መቻሏን ወጣት መዲና ገልጻለች።
ይሁንና በአቡዳቢ የአወሊያ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ተፈጻሚ አለመሆኑን የገለጸችው መዲና፤ ጠበቃውም ሆነ የኢትዮጵያ ቆንስላ፤ ስልክ ቢደወልላቸው እንኳን እንደማይመልስ አስረድታለች።
የፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ለመክፈት እንዳለውቻለች ያለመከለተችው መዲና ገንዘቡን ለማግኘት ያላት ተስፋ እየተሟጠጠ መምጣቱን ተናግራለች።