ነሀሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የአቶ መለስ ዜናዊን ከዚህ አለም በሞት መለየት ተከትሎ፣ መንግስት በይፋ በየከተማው ሙሾ እአስወረደ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ የአዲስ አበባ ፖሊሶች “አባይን የደፈረው መሪ” የሚል ጽሁፍ ያለበትን የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ በፒያሳ ጎዳናዎች ላይ ፣ በ5 ብር ሲሸጡ የተገኙ የጎዳና ላይ አዟሪዎች በፖሊስ ተይዘው የሚሸጡዋቸውን ፎቶዎች እንዲቀሙ ተደርጓል።
አንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ለዘጋቢያችን እንደገለጡት ከትናንት ጀምሮ ” አባይን የደፈረ ” በሚለው ፎቶ ጀርባ ላይ “ኢህአዴግን ግን አይወክልም” የሚል የጽሁፍ መልእክት በብዛት ተጽፎ መገኘቱ ነው።
የፖሊስ አባሉ እንዳሉት ፣ “ኢህአዴግን አይወክልም” የሚሉ ጽሁፎችን እየለዩ ከስርጭት ለማቆም ሙከራ እያደረጉ ሲሆን፣ ይህን አይነት ድርጊት የፈጸመው የትኛው አካል እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ ተጀምሯል ብለዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ ከመለስ በሁዋላ አዲስ ነገር ይመጣል ብለው ተስፋ የሚያደርጉ የመኖራቸውን ያክል ኢህአዴግ ስልጣኑን አጠናክሮ አፈናውን ይቀጥል ይሆን ብለው የሚሰጉ በብዛት መኖራቸውን ዘጋቢዎቻችን ገልጠዋል።
አንድ በአስኮ ወረዳ የሚኖሩ ሰው እንደተናገሩት በአቶ መለስ ሞት እግዚአብሄር አዲስ ነገር ይዞ እየመጣ ነው::
አቶ ለገሰ በበኩላቸው እርሳቸው በሚኖሩበት የደቡብ ክልል ህዝቡ በገንዘብ እየተደለለ እንዲያለቅስ መደረጉ አሁንም አለመማሩን ቢያሳይም መጪው ጊዜ የተሻለ እንደሚሆን ገልጠዋል
በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነው ወጣት በበኩሉ የመከራው ጊዜ እያለቀ ነው ብሎአል
በኦሮሚያ ክልል ነዋሪ የሆኑት ለዝግጅቱ ሲባል ስማቸው የተቀየረው አቶ አላምር በበኩላቸው በኢህአዴግ ውስጥ የሚታየው ትርምስ የኢትዮጵያን መጻኢ ጊዜ ሊወስን እንደሚችል ገልጠዋል
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በነገው ዕለት የከነጥበብ ባለሙያዎችና መገናኛ ብዙሃን ሐዘናቸውን የሚገልጹበት ፕሮግራም በኮምኒኬሸን ጽ/ቤት በኩል ተዘጋጅቶአል፡፡ የአቶ መለስ ያለበት ቲሸርት በ100 ብር እንድንገዛ እና ከጠዋቱ አንድ ሰዓት መስቀል አደባባይ ተገኙ ተብለናል ሲሉ ጋዜጠኞች ለኢሳት ተናግረዋል።
____________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide