ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከሰኔ 24 እስከ 26; 2004 በሰሜን አሜሪካ፥ ዳላስ ከተማ ከአርባ ከተሞችና ከተለያዩ አህጉራት የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት ጉባኤ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮችና የቀረቡ ሰነዶች ላይ ሶስት ቀናት የፈጀ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት ማቋቋሙን የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ጉባኤው “የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት፥ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበር ሁሉን አቀፍ ሕዝባዊ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ቅድመ‐ሁኔታዎች እንዲመቻች ፣ ጉበኤው “የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት” ተብሎ እንዲጠራ፥ እና ጊዜያዊ ጽ/ቤቱ በዋሽንግተን ዲሲ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፎአል።
በጉባኤው ከተገኙት ታዛቢዎች እና ተሳታፊዎች መካከል በቅርቡ በኦታዋ፥ ካናዳ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጐ ( ተወካዮች የሽግግር ምክርቤቱ በመመስረቱ የተሰማቸውን ደስታ ለጉባዔው ገልጸዋል። የሽግግር ምክርቤቱም ከሸንጎው እና ከሌሎችም የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲሁም የሲቪክ ማህበራት ጋር ውይይቶች በማድረግ ተባብሮ የሚሰራበትን ዘዴ እንዲፈጥር ጉባኤው አዲስ ለተመረጠው አመራር ሃላፊነት ሰጥቷል።
ጉባኤው የሽግግር ምክርቤቱን መተዳደሪያ ደንብ ካጸደቀ በኋላ አቶ ስለሺ ጥላሁንን ‐ አፈ‐ጉባዔ፤ ወ/ሮ መቅደስ ወርቁን ‐ ምክትል አፈ‐ጉባዔ፤ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱን ‐ ዋና ጸሃፊ አድርጎ መርጧል። ጉባኤው ስለሚከተለው የትግል ስትራቴጂ ይፋ አላደረገም ።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide