ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-የማእከላዊ ስታትስቲክስ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 85 ነጥብ 9 ሚሊዮን መድረሱን የገለጹ ሲሆን ፣ ከዚህ አሀዝ ውስጥ 81 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በገጠር የሚኖር ነው።
የ2005ዓም የህዝብ ብዛት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ2 ሚሊዮን ሰዎች ጭማሪ አሳይቷል።። የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ቁጥር በ500 ሺ ልቆ መገኘቱም ተመልክቷል።
የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገች ነው በማለት ቢናገርም ፣ በገጠር የሚኖው ህዝብ አሀዝ በአጼ ሀይለስላሴ ዘመን እና በደርግ ዘመን ከነበረው ሰፊ ልዩነት የለውም፡፡
በ1999 ዓ.ም የተደረገው የህዝብ ቆጠራ መረጃ እንደሚተነብየው ከሆነ ፥ በ2009 ዓ.ም አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ 94 ነጥብ 4 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ነው የተገመተው።