49 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የንጹህ ውሀ ተጠቃሚዎች አይደሉም ተባለ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-49 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የንጹህ ውሀና  ተጠቃሚዎች አይደሉም ፣ 75 ሚሊዮኑ ደግሞ ለንጽና መስጠበቂያ የሚሆን በቆ ውሀ አያገኙም

የሚሊኒየም የልማት ግቦችን አሳካለሁ በማለት ሌት ተቀን የሚናገረው የመለስ መንግስት ፣ ከ20 አመታት ከፍተኛ የውጭ እርዳታ በሁዋላ እንኳን የአገሪቱን የንጹህ መጠጥ ውሀ ሽፋንን ለማሻሻል አልቻለም።

ዘ ግሪን የተባለ ዌይባሳይት በፎቶ ግራፍ አስደግፎ ባቀረበው ዘገባ 82 ሚሊዮን ከሚጠጉ ኢትዮጵያውያን መካከል ንጹህ ውሀ የሚያገኙት 33 ሚሊዮን የሚሆኑት ሲሆኑ  75 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ንጽህናቸውን ለመጠበቅ የሚያስችላቸው ውሀ አያገኙም።

አመታዊ የሰዎች ገቢ 100 ደላር ብቻ በሆነባት ኢትዮጵያ ልጆች ውሀ ለማግኘት በየቀኑ 6 ሰአታትን ማጥፋት አለባቸው። 

አብዛኛውን ደሀ ህዝብ ንጹህ የመጠጥ ውሀ ተጠቃሚ በማድረግ የሚሊኒየም የልማት ግቦችን አሳካለሁ የሚለው መንግስት ፣ አሁን በሚታየው ተጨባጭ እውነታ፣ ከፕሮፓጋንዳ ባለፈ ተጨባጭ ስራ አለመስራቱን የሚያሳይ ነው የሚሉ አስተያየቶች ቀርበዋል።  

በአለም ደረጃ 1 ቢሊዮን የሚሆነው ህዝብ የንጹህ ውሀ ተጠቃሚ አይደለም።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide