20 የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አሁንም እንደታሰሩ ነው

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በቅርቡ በድሬዳዋ ከምግብ ጋር በተያያዘ ተነስቶ በነበረው ግጭት ታስረው ከነበሩት መካከል 300 የሚሆኑት ሲፈቱ አሁንም 20 ተማሪዎች ታስረዋል።

የዩኒቨርስቲው ምንጮች እንደገለጡት የፌደራል ፖሊስ አባላት በጊዜው በተማሪዎች ላይ ካደረሱት ከፍተኛ ድብደባ በተጨማሪ የተማሪዎችን ሞባይሎች ሳይቀር መወሰዳቸው ታውቋል።

በእለቱ በተፈጠረው ችግር ግምቱ ከ150 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ወድሟል።

የግጭቱ መንስኤ ከምግብ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ የዩኒቨርስቲው ምንጮች እንደሚሉት የዩኒቨርስቲው ዲን ባለፈው አመት 17 ሚሊዮን ብር ከምግብ ወጪ ቀንሰው ተመላሽ በማድረጋቸው መሸለማቸው ታውቋል።