117ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ዝግጅት በሄግ ፣ ኔዘርላንድስ ተካሄደ

የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ በስፍራው ተገኝቶ ያጠናቀረው ዘገባ እንዳመለከተው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የጣሊያንን ወራሪ ሀይል ድባቅ በመምታት የኢትዮጵያን ነጻነት ያስከበሩበትን 117ኛውን የአድዋ ድል፣ የተለያዩ ምሁራን በአካል በተገኙበትና በስካይፕ በተደረገ ንግግር ታስቦ ውሎአል።

የቀድሞው የህወሐት መስራች እና መሪ የነበሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ እና ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ በአካል ፣ ፕ/ር ጌታቸው መታፈሪያ እና አቶ ኪዳኔ አለማየሁ   ደግሞ ከአሜሪካ በስካይፕ  ስለአድዋ ድል ገለጻ አድርገዋል።

የኢትዮጵያውያን ማህበር በሆላንድ  ባዘጋቸው ዝግጅት ታዳሚዎች ለተናጋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማቅረብ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

በእለቱ የተለያዩ  ግጥሞችና አዝናኝ  ዝግጅቶች ቀርበዋል።