ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደትግል ቦታ መመለሳቸው ታወቀ

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2008)

በዩኤስ አሜሪካና አውሮፓ ለሳምንታት ቆይታ ያደረጉት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትግል ስፍራ መመለሳቸው ታወቀ። ማክሰኞ አስመራ የገቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአመሪካና አውሮፓ ከተሞች ከኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አቀባባል እንደተደረገላቸው ይታወቃል።

በዩ ኤስ አመሪካ ዋሽንግተን ዲሲና ሲያትል ከተሞች እንዲሁም በአውሮፓ ኦስሎ ጄኔብና ፍራንክፈርት ከኢትዮጵያውያን ጋር የተወያዩትና ከፍተኛ አቀባበል የተደረገላቸው የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በፍራንክፈርት በአነስተኛ ቁጥር የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ስለህወሃት ጀግንነት ሲገልጹና እሳቸውን ሲቃወሙ ታይተዋል። በቁጥር 30 የሚሆኑ የህወሃት ደጋፊዎችን አልፈው በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ተሰባሰቡበት አዳራሽ የገቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ “ወያኔዎች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣት መጀመራቸው ትግላችን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት መሸጋገሩን ያሳያል” ማለታቸው ተመልክቷል።