ግንቦት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ተጠርጥሮ ከሁለት ዓመታት በላይ በእስር ሲንገላታ የነበረው የደ-ብርሃን ብሎግ ተባባሪ ጦማሪ ዘላለም ወርቅአገኘሁ አምስት ዓመት ከአራት ወራት እስራት ተፈርዶበታል። አቃቤ ሕግ በዘላለም ወርቅ አገኘሁ ላይ ያቀረበበት ክስ በሽብርተኝነት ከተፈረጀው ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር በማበር በመንግስት ላይ አመጽ ማነሳሳት የሚል ነው።
በዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሽበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሽዋስ አሰፋ፣ ዮናታን ወልዴ፣ አብረሃም ሰሎሞን፣ ሰሎሞን ግርማ፣ ብርሃኑ ደጉና አቶ ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው። በሁሉም ላይ የቀረበባቸው ክስ የሽብረተኝነት ክስ ቢሆንም ብዙዎቹ ከአንድ አመት በላይ ለሆነ ጊዜ ከታሰሩ በሁዋላ በነጻ ተሰናብተዋል።
ዘላለም በህዝብ አስተዳደር የማስተርስ ትምህርቱን እያጠናቀቀ በላበት ወቅት መያዙ ይታወቃል።